
በ11ኛ ሳምንት የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ድሬዳዋ ከነማን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
የኢትዮ-ኤሌክትሪክን የማሸነፊያ ጎሎች ህዳት ካሱ በ31ኛው እና ማህሌት ምትኩ በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
ድሬዳዋ ከነማን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ጎል ብዙነሽ ሲሳይ በ86ኛው ደቂቃ አስቆጥራለች።
ኳስን ተቆጣጥሮ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመድረስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ብልጫ የነበረው ሲሆን ድሬዳዋ ከነማ በበኩሉ በመልሶ ማጥቃት ጎል ለማስቆጠር ጥረት አድርጓል።
የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የመሀል ተከላካይ የሆነችው ባንቺይርጋ ተስፋዬ የጨዋታው ኮከብ በመሆን ተሸልማለች።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ20 ነጥብ እና በስምንት ንፁህ ጎል ሊጉን በጊዜያዊነት እየመራ ይገኛል።
በ12ኛ ሳምንት መርሃግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመጪው ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከሲዳማ ቡና ጋር የሚጫወት ይሆናል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



