አቃቂ-II-ደብረዘይት-III-ዱከም-II-ሞጆ-II እና ጊኒቺ II ማከፋፈያ እና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ውጤት

የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ለአዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ኃይል ማቅረብ ነው። በአሁኑ ጊዜ ከ 600 ሜጋ ዋት በላይ የኃይል ጥያቄ አለ፡፡ ደብረዘይት ከተማ እና በአቅራቢያው ያሉ ከተሞች የሀገሪቱ ዋንኛ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች በመሆናቸው በቅርብ ጊዜ ውስጥ የኃይል ፍላጎቱ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል። በዚህ አካባቢ ላሉት ኢንዱስትሪዎች በ45 ኪሎ ቮልት፣ 66 ኪሎ ቮልት፣ 132 ኪሎ ቮልት እና 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች በመጠቀም ኃይል ለማቅረብና ፍላጎቱን ለማርካት ያልተቻለው በእርጅና እና በአቅም ውስንነት ምክንያት ነው።

ይህ ፕሮጀክት በደብረዘይት ከተማ እና አካባቢው እያደገ የመጣውን የነባር ደንበኞች ፍላጎት በማሟላት ነባሩን ማከፋፈያ ጣቢያ እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ከመልካ ዋከና እና ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የመነጨውን ኃይል በ230 ኪሎ ቮልት እና በ132 ኪሎ ቮልት ወደ ምስራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል ለማቅረብ የግንኙነት መንገድ ሆኖ ያገለግላል።

Scroll to Top