ጳጉሜን 4 — የሕብር ቀን

የኤሌክትሪክ ኃይልና የማህበራዊ አገልግሎት ተደራሽነት 💡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በማቋቋሚያ ደንቡ ከተሰጠው ኃይል የማመንጨት፣ የመነጨውን የማጓጓዝ እና ማከፋፈያ ጣቢያ የማድረስ  ተልዕኮ ብቻ ሳይሆን መሰረተ ልማቶቹ በሚገኙበት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክና የንጹህ ውሃ አቅርቦት ተጠቃሚ በማድረግ የማህበራዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማገዝ የተቋማችን ዋና የማህበራዊ ፍትህ መርህ ነው።
⚡️ በኮይሻ እና ጊቤ 3 አካባቢ
ከኮይሻ ፕሮጀክት ግራና ቀኝ ለሚገኙ የኮንታና ጎፋ ዞን ማህበረሰቦች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት እንዲሁም በጊቤ 3 አካባቢ በዳውሮ እና ወላይታ ዞኖች ለሚገኙ 14 ቀበሌዎች 350 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የኃይል ተደራሽነት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
 
💧 በመልካ ዋከና እና አሉቶ፦ ለህብረተሰቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የጤናና ትምህርት ቤት ግንባታዎች ከማከናወን ባሻገር ከ550 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 12 ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ አድርጓል።
 
🔌 በሶዶ፣ በለስ እና ተከዜ፦ በሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ ዙሪያ ለሚገኙ 12 ቀበሌዎች ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የኤሌክትሪክ መስመር የተዘረጋ ሲሆን፣ በበለስና ተከዜ አካባቢዎችም መሰል የኃይል ተደራሽነት የማረጋገጥ ስራዎች በመከወን ላይ ናቸው።

Scroll to Top