
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች መካከል በተሰጠው የተግባር ፈተና ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 10 ስማችሁ የተገለጸው ተወዳዳሪዎች ከግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የሰው ኃይል ምደባ ቢሮ በመገኘት የትምህርት ማስረጃ፣ የስራ ልምድ ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ ቀርባችሁ የቅጥር ሂደት እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡

