ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ብርሃን የሚፈነጥቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ! 🇪🇹⚡️🌍

ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ብርሃን የሚፈነጥቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ! 🇪🇹⚡️🌍

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD) የሀገራችንን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለምሥራቅ አፍሪካ አዲስ የኢኮኖሚና የኢነርጂ ትስስር ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል። ኢትዮጵያ ያላትን የታዳሽ ኃይል ፀጋ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በመለወጥ ቀጣናዊ ውህደትን የምታፋጥንበት ስትራቴጂካዊ መሣሪያም ሆኖ እያገለገለ ነው።

የግድቡ ስትራቴጂካዊ ሚና በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ይገለፃል፡፡

  1. የአፍሪካ የኃይል ቋት ማዕከልነት 🔋

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የኃይል ቋት ማዕከል በመሆን ለጎረቤት ሀገራት አስተማማኝና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ ኃይል ታቀርባለች። ይህ ኃይል ለኢትዮጵያም ሆነ ኃይል ከኢትዮጵያ ለሚገዙ ወገኖች ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

  • ለኢትዮጵያ፦ ከግድቡ የሚመነጨው ኃይል ሙሉ በሙሉ ቢሸጥ በዓመት እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይገኛል። ይህም ከቡና ቀጥሎ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የመሆንዕድል እንዳለው ያሳያል።
  • ለጎረቤት ሀገራት፦ እንደ ሱዳን፣ ኬንያ እና ጅቡቲ ያሉ ሀገራት በነዳጅ የሚመነጭ ውድ ኤሌክትሪክ የሚጠቀሙ ሀገራት ከኢትዮጵያ የሚገኘውን ታዳሽ ኃይል በመጠቀም ወጪያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንሱ እና ከካርቦን ልቀት ነፃ የሆነ ኢኮኖሚ እንዲገነቡም ይረዳቸዋል።
  1. የኢኮኖሚና የመሠረተ-ልማት ትስስር 🏗

የኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችሉ ግዙፍ የድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ተዘርግተዋል። ይህም ቀጣናውን በአንድ የኢኮኖሚ ሰንሰለት የማስተሳሰር ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

  • የኢትዮ -ኬንያ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር፦ ባለ 500 ኪሎ ቮልት (kV) የሆነው ይህ መስመር እስከ 2 ሺህ ሜጋ ዋት ድረስ በማጓጓዝ ኢትዮጵያን ከደቡብ አፍሪካ የኃይል ቋት (SAPP) ጋር ለማገናኘት መሠረት ነው።
  • የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ትስስር መፋጠን፦ አስተማማኝ ኃይል መኖሩ በቀጣናው የሚገነቡ እንደ አዲስ አበባ-ጅቡቲ ያሉ የኤሌክትሪክ ባቡሮች በብቃት እንዲሰሩ በማድረግ የንግድ ልውውጥን ያቀላጥፋል።
  1. ጂኦ-ፖለቲካዊ መረጋጋትና ሰላም 🤝

የኢኮኖሚ ትስስር ሲጠናከር በሀገራት መካከል ያለው የሠላም ዋስትና ይጨምራል። አንዱ ሀገር ለሌላው የኃይል አቅርቦት፣ ሌላኛው ደግሞ ለዚህ ኃይል ገበያ ሲሆን “የጋራ ተጠቃሚነት” (Win-Win) መንፈስ ይነግሳል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለምሥራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት አስተማማኝ የኃይል ምንጭ ሆኖ ያገለግላል። ጎረቤት ሀገራት ታዳሽና ርካሽ ኃይል ሲያገኙ ፋብሪካዎቻቸው ይስፋፋሉ፤ ይህም ለአፍሪካ አህጉራዊ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳው የጎላ ነው።

የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያና አፍሪካን ዛሬ ላይ በጋራ እንገነባለን!

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top