የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው እለት ባከበረው የተቋም ቀን የተለያዩ የፈጠራና አሰራርን የሚያዘምኑ ሥራዎችን በማከናወን አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር እና ተቋሙን ከተጨማሪ ወጭ በመታደግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡



በዚህም ባለሙያዎቹ ባከናወኑት ሥራ ተቋሙን ከ374 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማዳን የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚሁም መሠረት
ፍቅረዮሐንስ ታደሰ – በኖዝል ፊክስ የፈጠራ ሥራ በማከናወንና 2 ሚሊዮን ብር በማዳን፤
ፋንታሁን እስከዚያው – በጀኔሬተር የላይኛውና ታችኛው ጋይድ ቢሪን ላይ የማሻሻያ ሥራ በማከናወንና 2 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ በማስቀረት፤
ይስሃቅ ወልደየስ – የኢኪዩፕመንት ሎግ ሲስተም በመስራትና 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ በማዳን፤



ገብረመድህን ሐጎስ – የጀኔሬተር የታችኛውና የላይኛው ጋይድ ቢሪንግ የማሻሻያ ሥራ በማከናወንና የ10 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ በማዳን፤
ጌታቸው አለነ- የጀኔሬተር የታችኛውና የላይኛው ጋይድ ቢሪንግ የማሻሻያ ሥራ በማከናወንና 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ በማስቀረት፤
ቢኒያም ጸጋዬ እና ተመስገን ተክለብርሃን- ሳውዝ ክላውድ ሶፍትዌርን በማበልፀግና 8 ነጥብ 36 ሚሊዮን ብር በማስቀረት፤
ወ/ሪ ትአይመን ተልሰም፣ አቶ እያዩ ደሴ እና ደሳለኝ ተገኝ – ኢኢፒ ማስተር ሶፍት ዌር በማልማትና 48 ነጥብ 15 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ በማዳን፤

ዳንኤል አዳነ- በፓወር ትራንስፎርመር ጥገና ተቋሙን የ128 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ በማዳን፤
ሮቤል ቸርነት- ተቋሙ እየተገበረ ባለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራ የኢ ሰርቪስ ሲስተምን በማልማት ተቋሙን 163 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ከተጨማሪ ወጪ በማዳን፤ እያንዳንዳንዳቸው ከ50 እስከ 100 ሺህ ብርና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


