የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የተቋሙ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻን ጨምሮ ሁሉም ሥራ መሪዎችና የዋና መ/ቤት ሠራተኞች በተገኙበት በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መገምገም ጀምሯል።የግምገማ መድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የኦፕሬሽን፣ የፕሮጀክትና ሌሎች ተቋማዊ ሥራዎች እንዲሁም የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

በበጀት ዓመቱ ያለፉት ዘጠኝ ወራት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የአይሻና የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን አስመርቆ ወደ ሥራ በማስገባት ትልቅ ታሪክ የተመዘገበበት መሆኑን ተገልጿል።በተለያየ የግንባታ ሂደት ላይ በሚገኙ የኃይል መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ቀጣይነት ያለው መሻሻል መመዝገቡንም በመድረኩ ላይ ተብራርቷል።
ተቋሙ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ባሻገር ነባር የኃይል መሠረተ ልማቶችን በማዘመንና አቅማቸውን በማሳደግ በኩልም ቁልፍ ሥራዎች መከናዎናቸውም ተነግሯል።በበጀት ዓመቱ ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኪሳራ ወጥቶ ትርፍ የተመዘገበ ሲሆን ለዚህ ስኬት የመንግስት ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሮች የራሳቸው ድርሻ እንደነበራቸው ተገልጿል።በግምገማ መድረኩ የተቋሙን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የኮርፖሬት ፕላኒንግ ተወካይ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያለውአይቀር ማንደፍሮ እየቀረበ ይገኛል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


