የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ባከበረው የተቋም ቀን በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ማመንጫ ጣቢያዎች፣ ሪጂኖችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁመው ኃይል የማመንጨት ሥራቸውን እያከናወኑ ለሚገኙ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ዕውቅና ሰጥቷል።
በዚሁ መሰረት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ጊቤ 3 እና ገናሌ ዳዋ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እንዲሁም የሰሜን ምሰራቅ 1፣ መካከለኛ 2 እና ምስራቅ 2 ሪጅኖች በኃይል ማመንጨት፣ማስተላለፍ እና ማከፋፈል የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገባቸው የተሽከርካሪ፣ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።




በተመሳሳይ በለስ፣ ጢስ ዐባይ፣ ፊንጫ እና አመርቲ ነሼ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በአካባቢያቸው ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ ተቋቁመው ኃይል የማመንጨት ሥራቸውን በብቃት በመወጣታቸው በልዩ ሁኔታ የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀትና የተሽከርካሪ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
በፕሮጀክት አፈፃፀም በኩልም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ኮይሻ የውሃናአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በተጨማሪም ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፣ ገንዳ አርባ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ ለገጣፎ ኮምቦልቻ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የሽቦ ቅየራ ሥራ፣ በቆጂ እና ደብረ ታቦር ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች የዋንጫና የምሽክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።





