
በአዳማ ቁጥር ሁለት የማከፋፈያ ጣቢያ የተተከለው ተጨማሪ ትራንስፎርመር ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን አስታወቀ።
የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት በአዳማ የሚስተዋለው የኢንዱስትሪና የከተማ መስፋፋት የኃይል ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል።
ማከፋፈያ ጣቢያው እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ማስተናገድ የማይችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የአቅም ማሳደግ ሥራ መስራት እንዳስፈለገ ተናግረዋል።
ጣቢያው በ132/15 ኪሎ ቮልት አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፔር ትራንስፎርመሮች እንደነበሩት ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
ለአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ በ33 ኪሎ ቮልት አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፔር ተጨማሪ ትራንስፎርመር መተከሉን ገልፀዋል።
በሪጅኑ በራስ አቅም የተከናወነው የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ ሥራ የጣቢያውን አቅም በ50 በመቶ ከማሳደግ ባለፈ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
