የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና ቀን “ጤናማ የሥነ-ልቦናና ማህበራዊ የሥራ አካባቢን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በተቋም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በውይይት እየተከበረ በሚገኘው የሥራ ደህንነትና ጤና ቀን በዋናነት በሥራ ገበታ ላይ እያሉ በተለያዩ አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሠራተኞች መታሰቢያ እንዲሆን ታስቦ የተሰናዳ ነው።


ማንኛውም ሠራተኛ የዕለት ተግባሩን አከናውኖ ወደ ቤቱ በሠላምና በጤና የመመለስ ሙሉ መብት ቢኖረውም አሁንም ድረስ የሥራ ቦታዎች ላይ ተግዳሮቶች እንደሚታዩ በመድረኩ ተገልጿል።
በተለይም ደህንነቱና ጤንነቱ ያልተጠበቀ የሥራ አካባቢ፣ የእውቀትና የክህሎት ክፍተት እንዲሁም ደካማ የሙያ ደህንነት አጠባበቅ ባህል ለሠራተኞች ጤና ጉድለት፣ ለአካል ጉዳትና ለሞት መጋለጥ በምክንያትነት ተጠቃሽ ናቸው።
ሚያዚያ 20 ቀን የተከበረው የዘንድሮው የሙያ ደህንነትና ጤንነት ቀን፣ ያለፉትን አፈጻጸሞች በመገምገም እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ላይ ያተኮረ ነው።
በተቋም ደረጃ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ አንድም ሠራተኛ በሥራው ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስበት ጥንቃቄን እናስቀድም የሚል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡


