10 ሰዓታት የፈጀው የጥገና ሥራ በስኬት ተጠናቋል

10 ሰዓታት የፈጀው የጥገና ሥራ በስኬት ተጠናቋል

10 ሰዓታት የፈጀው የጥገና ሥራ በስኬት ተጠናቋልከትናንት በስቲያ በእሳት አደጋ ምክንያት በጊዜያዊነት አገልግሎት መስጠት ያቋረጠውን የድሬዳዋ ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ መስመር የማዛወር ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ።

በዘርፉ የምስራቅ አንድ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ እንደገለፁት ትናንት ምሽት ከ1:00 ሰዓት እስከ ሌሊት 11፡00 ከሁርሶ ወደ ድሬዳዋ አንድ፣ ወደ ሀረር እና ጅግጅጋ የሚሄዱ መስመሮችን የማዛወር ሥራ ተሰርቷል፡፡

ዛሬ ረፋድ መስመሩን የመፈተሽ ሥራ ተከናውኖ ወደሁሉም አካባቢዎች ኃይል እንደደረሰ መረጋገጡን ገልፀዋል።

የሁርሶ ማከፋፈያ ጣቢያ ጉዳት እንዳጋጠመው ተደርጎ የተሰራጨው ዘገባ የሀሰት መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ከሁርሶ ማከፋፈያ ጣቢያ ተጨማሪ ወጪ መስመር በማዘጋጀት ችግሩ መፈታቱን አስታውቀዋል፡፡

ፈታኝ የሆነው የመስመር ማዛወር ሥራ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟቸው በነበሩ አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትዕግስት ስለጠበቁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top