የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በኃላፊነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በኃላፊነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በኃላፊነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ ይገባልሁሉም የቀበሌ እና የወረዳ አመራሮች በየአካባቢያቸው የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በኃላፊነት ስሜት እንዲጠብቁ የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አሳሰቡ፡፡

የነቀምቴ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ምስጋኑ ቱሉ በበኩላቸው ያለ ኤሌክትሪክ የትኛውንም ዕቅድ ማሳካት ስለማይቻል በአጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮች ትናንት የምስራቅ ወለጋ ዞን እና ከዞኑ 18 ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮች እንዲሁም የነቀምቴ ከተማ አመራሮች በተሳተፉባቸው ሁለት መድረኮች ላይ በመገኘት ተቋሙን እየፈተኑት ስላሉት የመሰረተ ልማት ስርቆት ወንጀሎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት ደህንነት ቁጥጥር እና ክትትል ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደገለፁት በዞኑ ሥርቆት በሚበዛባችው ጉቶ ወረዳ – ሶረቃ ቀበሌ፣ ሁኪ ከተማ ዙሪያ፣ ሌቃ ዱለቻ ወረዳ፣ ደዴሳ አካባቢ፣ ጅማ አርጆ ወረዳ፣ ጊዳ አያና ወረዳ -ጉትን ከተማ አመራሩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 464/97 አንቀጽ 3 እንደተደነገገው ሁሉም የመንግስት መዋቅር የኤሌክትሪክና የቴሌኮም መሠረት ልማቶችን የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡

በአዋጁ የተጣለባቸውን ግዴታ በማይወጡ አመራሮች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያችል አሰራር መዘርጋት እንደሚገባም ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር የመሰረተ ልማቶቹ በሚጠበቁበት ሁኔታ የተጀመረው ወይይት በመላው ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በተቋሙ የንብረት እና ጠቅላላ አግልግሎት ዘርፍ የንብረት አስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ በበኩላቸው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ረጅም ኪሎ ሜትሮችን ስለሚያቆራርጡ የመሰረተ ልማቱን መጠበቅ የሁሉንም ተሳትፎ ይፈልጋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ከማህበረሰቡና በየደረጃው ከሚገኙ የመስተዳድር አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው አመራሩ በኃላፊነት ስሜት እንዲሰራ ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡

ምክትል አስተዳዳሪው አቶ ገመዳ ተረፈ በዞኑ በተዘጋጁ መድረኮች ላይ ለተሳተፉ ከ18 ወረዳ ለተውጣጡ አመራሮች እንደገለፁት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መጠበቅ ለሁሉም የተሰጠ በመሆኑ የቀበሌና የወረዳ አመራሮች በባለቤትነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዞኑ ሁኬ ከተማ በተካሄደ የተቀናጀ ፍተሻ ብዛት ያላችው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት አካላት በጋሪ ላይ የበየዱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማካሄድ ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

መሰረተ ልማቱን በማስጠበቅ ረገድ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት አመራሮቹ የተሻለ ወጤት ለማምጣት እንዲሰሩም አሳስበዋል፡፡

የነቀምቴ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ምስጋኑ ቱሉ በበኩላቸው ያለ ኤሌክትሪክ የትኛውንም ዕቅድ ማሳካት ስለማይቻል በአጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡

የህዝብ እና የመንግሥትን ንብረት የማይጠበቅ አመራር ካለ ተጠያቂነት እንደሚኖርበት ሊያውቅ ይገባል ብለዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top