ከ2011 ጀምሮ በነበሩት ባለፉት ሰባት ዓመታት በሀገራችን የኃይል ማመንጨትና መሠረተ-ልማት ግንባታ ላይ የተመዘገበው ውጤት እጅግ አስደናቂ ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ነው። አሐዞች እንደሚነግሩን ዘርፉ በየዓመቱ በአማካይ የ10% እድገት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።
⚡️ ዋና ዋና የስኬት አመልካቾች (2011 እስከ 2017)
💡 የኃይል ምርት መጠን፦ ከ15.3 ቴራዋት ሰዓት (TWh) ወደ 29.5 ቴራዋት ሰዓት በእጥፍ አድጓል።
💡 የማመንጨት አቅም፦ ከ4,500 ሜጋ ዋት (MW) ተነስቶ አሁን 9,760 ሜጋ ዋት ደርሷል።
💡 አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ፦ ከነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ወደ 75.4 ቢሊዮን ብር አድጓል።
💡 የውጭ ምንዛሬ ገቢ፦ ከቀጣናዊ የኃይል ሽያጭና ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚገኘው ገቢ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በታች የነበረ ሲሆን አሁን 338.7 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።
🇪🇹💡 ኢትዮጵያን በዓለም ልዩ የሚያደርጋት ምንድነው?
ሀገራችን አጠቃላይ የኃይል ምንጯን 100 በመቶ ወደ ታዳሽ ኃይል (Renewable Energy) ያሸጋገረች ጥቂት ከሚባሉ የዓለም ሀገራት ተርታ መሰለፏ ትልቅ ኩራት ነው። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፦
💡 17 የውኃ ኃይል ማመንጫዎችን፤
💡 5 የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን፤
💡 1 የጂኦተርማል (የከርሰ ምድር እንፋሎት) እና
💡 1 ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል የሚያመነጭ ጣቢያን ያስተዳድራል።
🏗⚡️ የመሠረተ-ልማት አውታራችን ስፋት፦
ከተለያዩ የኃይል ማመንጫዎች የተመረተው የኃይል ምርት 15,857 ኪሎ ሜትር የሰርኪዩት ርዝመት ባላቸው የማስተላለፊያ መስመሮችና የተለያየ የቮልቴጅ መጠን ባላቸው 148 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች (Substations) ባሉት ዘመናዊ የግሪድ ኔትወርክ ለተጠቃሚዎች እየደረሰ ይገኛል።
💡🇪🇹 የኢትዮጵያ ብርሃን ለቀጣናውም ትርፍ የሚሆን ብርታት እየሆነ ነው! 💡🇪🇹