ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የታደለችው የታዳሽ ኃይል ጸጋ እጅግ ግዙፍ መሆኑን ያውቃሉ?
እውነታው ምን ይላል?
📊 ኢትዮጵያ ያላት እምቅ አቅም፦ ከውሃ፣ ከፀሐይ፣ ከነፋስና ከከርሰ ምድር እንፋሎት (Geothermal) ምንጮች እስከ 150 ጊጋ ዋት (GW) ኃይል የማመንጨት አቅም አላት።
🏗 እስካሁን የለማው፦ ካለን አጠቃላይ አቅም ውስጥ እስካሁን ማልማት የቻልነው 9.5 ጊጋ ዋት (GW) ብቻ ነው። ይህ ማለት ካለን ጸጋ ጥቅም ላይ የዋለው 6.33% ብቻ ሲሆን፣ ቀሪው 93.67% ገና ያልተነካና ለልማት የሚጠበቅ መሆኑን ያሳያል።
ይህ አቅም ለሀገራችን ምን ትርጉም አለው?
- 🏭 የኢንዱስትሪ ሽግግርን ይደግፋል፤
ለአምራች ፋብሪካዎቻችንና ለኢንዱስትሪ ፓርኮች አስተማማኝና ርካሽ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል። - 💰 የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ያሰፋል፤
ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማግኘት የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ለማረጋገጥ ተጨማሪ አቅም ይፈጥርላታል። - 🌿 የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ያግዛል፤
ከብክለት ነጻ የሆነና የአካባቢ ጥበቃን ያገናዘበ ታዳሽ የኃይል ምንጭ ለመገንባት የተጀመረውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ እውን ለመሆን ያግዛል። - 💡 ለትውልድ ብርሃን ይሆናል፤
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልደረሳቸውን የገጠር አካባቢዎች ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይህንን እምቅ አቅም በስፋት በማልማት፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል!
ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ትበራለች!