በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች የተሻለ የግንባታ አፈጻጸምና የፋይናንስ ቁመና እንዲኖራቸው ሠራተኛው በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት በተቋሙ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ገለጸ።
ዘርፉ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ በሥሩ ከሚገኙ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ውድነህ የማነ እንደተናገሩት መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች ዙሪያ በመወያየት በቀሪ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ ነው።
እንደ ተቋም ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በራስ አቅም ለመስራት የፕሮጀክት ክትትልና አፈጻጸምን በማሻሻል ትርፋማነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በዘርፉ ስር የሚገኙ የአምስት መምሪያዎች እና የሁለት የሥራ ክፍሎች የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


