ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል

ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል

የአሸጎዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ለአካባቢው ማህበረሰብ የሥራ ዕድል መፍጠሩን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅና ተቀጣሪዎች ተናገሩ፡፡

ሥራ አስኪያጁ አቶ አብርሃም አባተ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በጥበቃና በተለያዩ የግንባታ ሥራዎች ለ70 ወጣቶች ጊዚያዊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

በመቐለ ከተማ ዙሪያ ነዋሪ የሆኑት አቶ ደስታ ገብሬ እንደተናገሩት ለብዙ ዓመታት በአናፂነት ሙያ ቢሰሩም የሚያገኙት ገቢ ከራሳቸው ልብስና ጉርስ አልፎ ቤተሰብን ለማገዝ ትልቅ ፈተና ሆኖባቸው ነበር።

የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቱ በአካባቢያቸው መጀመሩ የሥራ ዕድል ስለፈጠረላቸው የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደረዳቸው ተናግረዋል።

በፕሮጀክቱ በመስራት ላይ የሚገኘው አቶ መሐሪ ግርማይ በበኩሉ እርሱና ቤተሰቡ ኑሯቸውን የሚገፉት በትንሽ የእርሻ ሥራ በሚያገኙት ገቢ እንደነበር ጠቅሶ ፕሮጀክቱ በአካባቢው ከተጀመረ ወዲህ ግን የሥራ ዕድል እና ተጨማሪ ገቢ ማግኘቱን ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚያከናውናቸው የኃይል መሠረተ ልማት ግንባታዎች ለበርካታ ወጣቶች ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል።

የአሸጎዳ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በህዳር ወር 2016 ዓ.ም የግንባታ ሥራው የተጀመረ ሲሆን በ8 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top