በአዲስ ዌስት ማከፋፈያ ጣቢያ ጉዳት የደረሰበትን ትራንፎርመር በሌላ ለመተካት የማጓጓዝ ሥራው በጥንቃቄ እየተከናወነ ነው።
በማከፋፈያ ጣቢያው የሚቀየረውን ትራንስፎርመር ፈታቶ በሎው ቤድ እና በሦስት አይሱዙዎች የማጓጓዝ ሥራው በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተመራ ይገኛል።
ትራንስፎርመሩ በሚያልፍበት አካባቢ የሚገኙ የሥርጭት መስመሮችና ድልድዮች በማጓጓዝ ሥራው ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥሩ የቅየሳ ባለሙያዎች አስቀድመው ከፊት በመንቀሳቀስ መንገዶችን ምቹ የማድረግ ሥራ በመስራት ላይ ናቸው።
ትራንስፎርመሩን የጫነው ሎው ቤድ በቀን በአማካይ ከ50 እስከ 70 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ላይ ነው።
ከዚህ በተጓዳኝ ትራንስፎርመሩን የመጠገን ሥራው በገላን ወርክሾፕ በመሰራት ላይ ይገኛል።
የትራንስፎርመር ማጓጓዝ ሥራ ፈታኝና ጥንቃቄ ከሚፈልጉ ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑን ምን ያህል ያውቃሉ?


