መስመሩ ተጠግኖ ወደ አገልግሎት ተመልሷል

መስመሩ ተጠግኖ ወደ አገልግሎት ተመልሷል

ከለገጣፎ -ቃሊቲ ከተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወድቀው የነበሩ አምስት የብረት ምሰሶዎች ጥገና ተጠናቆ መስመሩ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የማዕከላዊ ሪጅን አንድ አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደተናገሩት የመስመሩ ወደ አገልግሎት መመለስ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በከፊል ቀንሶ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት መመለስ አስችሏል።

የብረት ምሰሶ መሠረት ኮንክሬት ስራ፣ የምሰሶ ብረት ገጠማና የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ ሥራዎችን በማጠናቀቅ መስመሩ ወደ ኦፕሬሽን እንዲገባ መደረጉንም ነው ዳይሬክተሩ ያስታወቁት።

የጥገና ሥራው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ያላሰለሰ ሁለንተናዊ ድጋፍ ላከናወኑ ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ለወረዳ አመራሮች እና ለፀጥታ አካላት ዳይሬክተሩ ምስጋና አቅርበዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top