ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት!

ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት!

ውሃ ለኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ዋነኛውና ዋናው የኃይል ምንጭ ነው። በተለይም በውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረተው እያንዳንዱ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚጀምረው ከአንዲት የውሃ ነጠብጣብ በመጠራቀም በመሆኑ የውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዓት በኃይል ማመንጨት ሂደት ቁልፍ ሚና አለው!

ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ለኃይል ዘርፉ ያለው ወሳኝ ፋይዳ

  • የኃይል ብክነትን መቀነስ

በወቅታዊ የአየር ንብረት መለዋወጥና ያላግባብ በሚባክን የውሃ ሀብት ምክንያት የሚፈጠርን የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም መቀነስ ይከላከላል።

  • ዘላቂ የኃይል አቅርቦት

ግድቦች ሙሉ የማመንጨት አቅማቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እና ሥርዓት ባለው ሁኔታ እንዲጠቀሙ ያስችላል።

  • ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ

እያንዳንዷ የምትባክን የውሃ ነጠብጣብ በኃይል ማመንጨት ሂደት ላይ የምታሳድረው ተጽዕኖ በቀጥታ በመኖሪያ ቤቶች፣ በፋብሪካዎች፣ በንግድና በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ውጤታማ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም።

ስለሆነም አንድም ኪሎ ዋት ኃይል ሳናባክን ሙሉ አቅማችንን ለመጠቀም የሚያስችል የተቀናጀና ዘመናዊ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት ለህዝባችን ኃይል ማቅረባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!

Scroll to Top