የወልቂጤ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ከደንበኞች የሚቀርቡ የኃይል ጥያቄዎችን እየመለሰ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ።
ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙጀረብ የኑስ እንደተናገሩት ማከፋፈያ ጣቢያው ካለው 360 ሜጋ ዋት ኃይል ውስጥ 102 ሜጋ ዋት ኃይሉ ደንበኞችን ሲጠብቅ ቆይቷል፡፡
ጣቢያው ያለውን አቅም ለመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራው ሥራ አሁን ላይ እስከ 80 ሜጋ ዋት ኃይል የሚጠቀሙ ተጨማሪ ደንበኞችን ማግኘት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ከኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች መካከል የቢተን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድርጅት ሱፐርቫይዘር ሚስተር ጂየን ሊየን በበኩላቸው ከጣቢያው የጠየቁትን ኃይል በአጭር ጊዜ በማግኘታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ ለሰጣቸው ፈጣን ምላሽ እና ላደረገላቸው ትብብር አመስግነው በቀጣይም በመካከላቸው የሚኖረውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



