ጣቢያው የአካባቢውን የኃይል ፍላጎት ለመመለስ ችሏል

ጣቢያው የአካባቢውን የኃይል ፍላጎት ለመመለስ ችሏል

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሆለታ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደስራ ያስገባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች የተሟላ ኃይል  ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ።

ሥራ አስኪያጁ አቶ ጥላሁን አዘዘው እንደተናገሩት የሆለታ ማከፋፈያ ጣቢያ ለአቃቂ፣ ሰበታ እና ሱሉልታ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ለአካባቢው ነዋሪዎችና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩ አምራቾች በተሟላ መልኩ ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

ጣቢያው የተገጠመለት ጂ አይ ኤስ መቆጣጠሪያ፣ የስካዳ ሲስተም እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጣቢያው ኃይል ሳይቆራረጥ ደንበኞች ጋር ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ የጣቢያው የጥገና ባለሙያ ተዳቻ ገናሌ ተናግረዋል።

የጣቢያው መሳሪያዎች የኃይል መቋረጥ ሲኖር ችግሩ የደረሰበት መስመር እና የችግሩን ዓይነት እንዲሁም የችግሩን መጠን በመለየት መረጃን በቀላሉ መልሶ ለመጠገን እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
የካቲት 13  ቀን 2017 ዓ.ም

Scroll to Top