የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተደርጓል

የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተደርጓል

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ንግድ መድን ኤጀንሲ የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት አድርገዋል።

ስምምነቱ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች የፋይናንስ አቅርቦት ስጋት እንዳያጋጥማቸው ለባለሀብቶች ዋስትና ለመስጠት እና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በዘርፉ ያላቸውን እምነት ለማሻሻል የሚያስችል እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተነግሯል።

ስምምነቱ የፋይናንስ ስጋቶችን በመቀነስ የአልሚዎችን የክፍያ ደህንነት እና ወሳኝ የሆኑ መንግስታዊ  ተቋማትን ወቅታዊ ክፍያዎች ለማረጋገጥ እንደሚረዳም ተመላክቷል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ስምምነቱ ክፍያዎችን በወቅቱ ከማሳለጥ ባለፈ የፋይናንስ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ የኃይል ግዥ ስምምነቶችን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የብድር ብቃትን ለማሻሻል ያግዛል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ እያደገ ባለው የታዳሽ ሃይል ገበያ ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንደሚረዳ መገለፁን ካፒታል ጋዜጣ በማህበራዊ የትስስር ገፁ ዘግቧል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Scroll to Top