የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ያለመ ወይይት ከሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ጋር አካሂዷል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት በሥራ ተቋራጮች የአፈጻጸም ድክመት እንዲሁም ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ምክንያት በሚጓተቱ ፕሮጀክቶች ምክንያት ተቋሙ ለአላስፈላጊ ወጭና ለተደጋጋሚ የሕዝብ ቅሬታ እየተዳረገ ነው።
ተቋሙ ከፕሮጀክቶች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ለማሻሻል የመዋቅር ማሻሽያ ጭምር ማድረጉን ጠቁመዋል።
በግንባታ ላይ የሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ተቋሙ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በተቋሙ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ሲዓ በበኩላቸው ውይይቱ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮችን ምንጭ በመለየት መፍትኄዎችን ለማስቀመጥ እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።



ውይይቱ በግንባታ ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ከማገዙም በተጨማሪ በቀጣይ ግንባታቸው ለሚጀመሩ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚገኝበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የእቃ አቅርቦት፣ የጸጥታ ችግር፣ የካሳ ክፍያ፣ ስርቆት እና ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ችግሮች ለፕሮጀክቶች መዘግየት ምክንያት መሆናቸውን ሥራ ተቋራጮቹ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በሰጡት የማጠቃለያ ሃሳብ በሁሉም ወገን ለፕሮጀክቶቹ መዘግየት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በመቅረፍ ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ሥራ ተቋራጮች አደረጃጀታቸውን በማጠናከር፣ የሰው ኃይል እና የግብዓት አቅርቦታቸውን በማሻሻል ፕሮጀክቶችን በወቅቱና በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡
በቀጣይ መሰል ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተጠቁሟል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”






የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም