የወልቂጤ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን የማዘምን ስራ እየተሰራ ነው

የወልቂጤ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን የማዘምን ስራ እየተሰራ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወልቂጤ ባለ 230  ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያን የማዘመን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጣቢያው ሥራ ኃላፊ ሙጀረብ የኑስ ገልፀዋል።

ኃላፊው እንደገለፁት በማከፋፈያ ጣቢያው ዘመናዊ የጂአይኤስ መቆጣጠሪያ ቅየራ እና ወረቀት አልባ የኦፕሬሽን ሥራዎች ክትትል ሥራዎች ተጀምረዋል።

ማከፋፈያ ጣቢያው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚፈልጉ ደንበኞችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እንደተፈጠረለት ገልፀዋል።

እንደኃላፊው ገለፃ ማከፋፈያ ጣቢያው 360  ሜጋ ዋት የመጫን አቅም ያለው ቢሆንም አሁን ላይ ለደንበኞች እያቀረበ ያለው 158 ሜጋ ዋት ብቻ በመሆኑ ተጨማሪ ደንበኞችን እየጠበቀ ይገኛል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያው ከሰኮሩ ማከፋፈያ ጣቢያ በ230 ኪሎ ቮልት ኃይል ተቀብሎ ለሰበታ፣ ለሆሳዕናና ለወሊሶ ማከፉፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ለጉራጌና አካባቢው ማህበረሰብ ኃይል ያቀርባል።

ከዚህ በተጨማሪም ጣቢያው ለሊፍ የተፈጥሮ ውሃና ለዘቢዳር ቢራ ፋብሪካዎች  እንዲሁም ለወልቂጤ ዬኒቨርስቲ ኃይል እያቀረበ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ጣቢያውን በሙሉ አቅሙ ለመጠቀም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ከማዕከላዊ  ጉራጌ ዞን  አስተዳደር ጋር ጋር ምክክር እየተደረገ  እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top