የመልካ ዋከና የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 527 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረቱን የጣቢያ የኦፕሬሽን ክፍል ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ።
ሥራ አስኪያጁ አቶ ተክሉ ጎንፋ እንደተናገሩት ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 488 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት አቅዶ 527 ጊጋ ዋት ሰዓት አመንጭቷል።
ይህም ከዕቅዱ የ39 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም የ7 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን በበጀት ዓመቱ በጣቢያው የተከናወኑ የፍተሻና ጥገና ሥራዎች የተርባይኖችን የማመንጨት አቅም ማሳደግ መቻሉን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
ከሚያዚያ 1980 ዓ.ም ጀምሮ ኃይል በማምረት ላይ የሚገኘው የመልካ ዋከና የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 153 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው።



