የቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ አስተማማኝ ኃይል እያቀረበ መሆኑ አስታወቀ።
የማመንጫ ጣቢያው የጥገና ክፍል ኃላፊ አቶ ያፌት ተስፋዬ እንደገለፁት የማከፋፈያ ጣቢያው የምስራቁን የሀገራችን ክፍል ከዋናው ግሪድ ጋር የሚያገናኝ ነው።
እንደ አቶ ያፌት ገለጻ ጣቢያው ከመልካ ዋከና፤ ከአዳማ ንፋስ ኃይል ማመንጫ እና ከቃሊቲ ኃይል በመቀበል ለሁርሶ፣ ለአዳማ እና ለቃሊቲ ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል የሚሰጥ በመሆኑ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር የማመንጫ ጣቢያው በዕቅድ ላይ የተመሰረተ የጥገናና የፍተሻ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ጣቢያው ሲመሰረት ሰው የማይቆጣጠረው የነበረ ቢሆንም ዕድሜው እየገፋ ሲሄድ ግን የሠው ኃይል በመፈለጉ የማመንጫ ጣቢያው ያሉትን የኦፕሬሽን አና የጥገና ሠራተኞች በመመደብ ጭምር የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል።
ጣቢያው ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ከመስጠቱ ጋር ተያይዞ የማዘመንና የማስፉፊያ ሥራ የሚያስፈልገው መሆኑንም ተናግረዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

