ጣቢያዉ በዞኑ የተሰማሩ የኢንቨስተሮችን የኃይል ፍላጎት መልሷል

ጣቢያዉ በዞኑ የተሰማሩ የኢንቨስተሮችን የኃይል ፍላጎት መልሷል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወልቂጤ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ በጉራጌ ዞን  ለተሰማሩ ከ315 በላይ የሚሆኑ ኢንቨስተሮችን የኃይል ፍላጎት በተሟላ መልኩ መመለስ መቻሉን የዞኑ አስተዳደር የኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቁ፡፡

የመምሪያው ልዩ አማካሪ አቶ ዳርጌ ተረፈ እንዳስታወቁት የወልቂጤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአካባቢው መኖሩ ኢንቬስተሮችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው፡፡

በአካባቢው ሰላማዊ እና ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ከመኖሩ ባሻገር በቂ የኃይል አቅርቦት መኖሩ ባለሀብቶቹን በመሳብ በኩል ያለውን ዕድል ማስፋቱን ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ዳርጌ ገለፃ የኢንቨስትመንት ሥራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ ከኃይል አቅርቦት ጋር ለተገናኙ ችግሮች ማከፋፈያ ጣቢያዉ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የድርሻዉን እየተወጣ ነው፡፡

በአካባቢዉ እየተነቃቃ የመጣዉን ኢንቨስትመንት አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅርቡ የኢንዱስትሪ መንደር ለማቋቋም ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን አማካሪው ጠቁመዋል፡፡

ባለሀብቶች ዞኑ ባሉት የኢንቨስትመት አማራጮች ላይ ለመሰማራት ሲመጡ በአካባቢው ምንም ዓይነት የኃይል እጥረት እንደማይገጥማቸዉ ልዩ አማካሪው አረጋግጠዋል፡፡

የጉራጌ ዞን አስተዳደር በ10 ወረዳዎች እና በአምስት የከተማ መስዳድሮች የተዋቀረ ሲሆን አካባቢዉን ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድርግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top