በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው።
ግምገማው የሪጅኖችን የዘጠኝ ወራት ክንውን፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ የመፍትሄ ርምጃዎች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣዎች ላይ ያተኮረ ነው።
በግምገማው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ ተቋሙ እያደረገ ካለው ሪፎርም ጎን ለጎን የኦፕሬሽን ሥራዎችን በአግባቡ በማከናወን የተቋሙን ግቦች ማሳካት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ለሚደርሱ ጥፋቶች እና ሌሎች አስተዳደራዊ ክፍተቶችን ለማረም ተጠያቂነት ከማስፈን ጎን ለጎን ቀድሞ መከላከል ላይ ያተኮረ አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ለዚህም ሁሉም ሪጅኖች ከመስተዳድር አካላት እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ተቀራርቦ በመስራት እና ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት አስተማማኝ ኃይል ለህብረተሰቡ ማድረስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዘጠኝ ወራት ውስጥ የማስተላለፊያ መስመሮች፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በዝርዝር ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



