ጣቢያው ባለፉት ስድስት ወራት ከ226 ጊጋ ዋት ስዓት በላይ ኃይል አምርቷል

ጣቢያው ባለፉት ስድስት ወራት ከ226 ጊጋ ዋት ስዓት በላይ ኃይል አምርቷል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት ያለፉት 6 ወራት 226 ነጥብ 75 ጊጋ ዋት ሠዓት ማምረቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለጹ።

ሥራ አስኪያጁ አቶ ቴዎድሮስ በቀለ እንደገለጹት ጣቢያው ባለፉት 6 ወራት 246 ነጥብ 41 ጊጋ ዋት ስዓት ኃይል ለማምረት አቅዶ 226 ነጥብ 75 ጊጋ ዋት ሠዓት ኃይል በማምረት የዕቅዱን 92 በመቶ አሳክቷል።

በ2016 በጀት ዓመት የመጨረሻ ወራት በጣቢያው ግድብ ላይ የነበረው ውሃ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነሱ በግድቡ የተሻለ ውሃ ለመያዝ ሲባል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ወራት በአንድ እና ሁለት ዩኒት ብቻ እንዲሰራ በመደረጉ አፈፃፀሙ ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል።

በጣቢያው ላይ የቅድመ መከላከል፤ የትንበያና የሁኔታ አመላካች ጥገና ሥራዎች በእቅድ ተይዘው እየተከናወኑ በመሆኑና በግድቡ በቂ ውሃ በመኖሩ በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻለ ኃይል ለማምረት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ጣቢያው ያለምንም መልሶ ግንባታ ከ37 ዓመት በላይ በማገልገሉ በየጊዜው የተለያዩ ችግሮች እየተከሰቱ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቴዎድሮስ  ካሉት አራት ተርባይኖች አንዱ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የመልሶ ግንባታ ሥራ ለመስራት ከሩሲያ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸው ስምምምቱ ተፈርሞ በአፋጣኝ ወደ ሥራ እንዲገባ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በአራት ተርባይን 153 ሜጋ ዋት የማምረት አቅም ያለው የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

Scroll to Top