ጣቢያው በሙሉ አቅሙ ኃይል እንዲያመነጭ ርብርብ እየተደረገ ነው፤

ጣቢያው በሙሉ አቅሙ ኃይል እንዲያመነጭ ርብርብ እየተደረገ ነው፤

ጣቢያው በሙሉ አቅሙ ኃይል እንዲያመነጭ ርብርብ እየተደረገ ነው፤የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ ኃይል እንዲያመነጭ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀኔሬሽን ኦፕሬሽን ቴክኒካል ድጋፍ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱ ይማም ጣቢያው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት አቁሞ የቆየውን መደበኛ የኦፕሬሽን ሥራ ቢጀምርም በሙሉ አቅሙ እየሰራ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጣቢያው በሙሉ አቅሙ የኦፕሬሽን ሥራውን እንዲያከናውን ለማስቻል በሦስት ምዕራፍ የተከፈለ የጥገናና የፍተሻ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሥራው ከፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ምዕራፍ አንድ ቨርኔት እንዲሁም ምዕራፍ ሁለትና ሦስት ጀነራል ኤሌክትሪክ በተሰኙ ኩባንያዎች እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

ሥራውን ለማከናወን ከአጋር ድርጅቶች በቀረበ ምክረ ኃሳብ መሰረት የሳይት ምልከታ በባለሙያዎች መከናወኑንን የተናገሩት አቶ አብዱ በምልከታው መሰረትም ጣቢያው በሙሉ አቅሙ የኦፕሬሽን ሥራውን እንዲያከናውን የሚያስችል የመለዋወጫ እቃዎችን በመለየት እቃዎቹን ከአምራች ፋብሪካዎች ለመግዛት በሂደት ላይ እንደሚገኙም አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም በጣቢያው ጋልልዮ የተባለው የስካዳ መቆጣጠሪያ ጋር ተያይዞ ያለው ሲስተም በአሁን ባለው ሞዴለ የማሳደግ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ አብዱ ገለጻ ጣቢያውን ወደ ሙሉ የኦፕሬሽን ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ ችግር የነበረውን የባትሪ መለዋወጫ እቃ ለመቅረፍ የአገር ውስጥ ጨረታ ወጥቶ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር የውል ስምምነት መፈረሙን ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም በጣቢያው ያለውን የውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ጨረታ ወጥቶ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ ኃይል ማመንጨት ሲጀምር በሀገሪቱ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ እንደሚያግዝ የገለጹት ኃላፊው ለዚህም ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 120 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡

Scroll to Top