ጣቢያው ለጅግጅጋና አካባቢው ነዋሪዎች አስተማማኝ ኃይል እያቀረበ ነው

ጣቢያው ለጅግጅጋና አካባቢው ነዋሪዎች አስተማማኝ ኃይል እያቀረበ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጅግጅጋ ማከፋፈያ ጣቢያ ለአካባቢው ነዋሪዎች እና በከተማዋ ዙሪያ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝ የጣቢያው ኃላፊ አስታወቁ፡፡

የጣቢያው ኃላፊ አቶ ደምለው ተሾመ እንዳስታወቁት 60 ሜጋ ዋት የመጫን አቅም ያለው የማከፋፈያ ጣቢያው በስምንት ወጪ መስመሮች ለክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋና ለአካባቢው ከተሞች 30 ሜጋ ዋት ኃይል እያቀረበ ይገኛል፡፡

ጣቢያው በ 33 ኪሎ ቮልት ለፋፈም፣ ለቶጎ ጫሌ፣ ለቀብሪበያህ፣ ለጭናክሰን እና በአከባቢው ለሚገኙ ከተሞች አስተማማኝ ኃይል እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጣቢያው ካለው አቅም 30 ሜጋ ዋት የሚሆነው ደምበኞችን በመጠባበቅ ላይ በመሆኑ  ባለሀብቶች በአቅራቢያቸው የተዘጋጀላቸውን ኃይል እንዲጠቀሙበት ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እንደ አቶ ደምለው ገለፃ ጣቢያው አንድ ባለ 25 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመር እና ሁለት ባለ 31 ነጥብ 5 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች አሉት፡፡

የጅግጅጋ ማከፋፈያ ጣቢያ በ132 ኪሎ ቮልት ከሐረር ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ተቀብሎ መልሶ በ132 ኪሎ ቮልት ለደገሀቡር ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ያስተላልፋል፡፡

ጣቢያው ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top