ጣቢያው ለበርካታ ከተሞች እና ፋብሪካዎች ኃይል በማቅረብ ላይ ነው

ጣቢያው ለበርካታ ከተሞች እና ፋብሪካዎች ኃይል በማቅረብ ላይ ነው

የደብረብርሃን ቁጥር 2 ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአቅራቢያው ላሉ ከተሞች እና ፋብሪካዎች ኃይል በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ የጣቢያው ኃላፊ አስታወቁ፡፡

ኃላፊው አቶ ዳኜ ይታገሱ እንደተናገሩት ጣቢያው ለደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ በርካታ ፋብሪካዎች፣ ለደብረብርሃን፣ ለእነዋሪ፣ ደነባ፣ መንዲዳ፣ ጅሁር፣ ሀገረማርያም፣ ሸኖ እና ጫጫ ከተሞች በቀን እስከ 48 ሜጋ ዋት ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በዳታ ማይኒንግ ለተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎች በቀን እስከ 20 ሜጋ ዋት ኃይል በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ጣቢያው በ 33 ኪሎ ቮልት ዘጠኝ ወጪ መስመሮች እንዲሁም በ15 ኪሎ ቮልት ስምንት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡

በቅርቡ ወደ ምርት ሥራ ይገባል ተብሎ ለሚጠበቀው የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ በ 230 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር ለመዘርጋት ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑንም ነው አቶ ዳኜ ያብራሩት፡፡

በ2011 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የደብረብርሃን ቁጥር 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሁለት ባለ 125 ሜጋ ቮልት አምፒር እና ሁለት ባለ 63 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች አሉት፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top