ገደሉን ተሻግረን በሕዳሴ ገድል አትመናል   – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ገደሉን ተሻግረን በሕዳሴ ገድል አትመናል   – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የገጠሙንን ፈተናዎችና ችግሮች ተጋፍጠን ገደሉን ተሻግረን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በማጠናቀቅ ገድል አትመናል ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህን የተናገሩት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ሕዳሴ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ የመጭው ንጋት ማብሰሪያ እንዲሁም ለመላ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ታሪክ ሆኖ የሚኖር ገድል ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሕዳሴን የሰራችው የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ጨምሮ አፍሪካውያንን በኃይል ለማስተሳሰር እንጂ የጎረቤት ሃቅን ለማስቀረትና ለመጉዳት አለመሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

ስለሕዳሴ በመናገር ጊዜ አናባክንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴን ግድብ የሚስተካከል ለሠላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒኩሌር ኃይል ማመንጫን ጨምሮ የአየር ማረፊያ ግንባታ፣ የማዳበሪያ እና የጋዝ ፋብሪካዎችን ሥራ በቅርቡ እንደምታስጀምርም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን በሁሉም አቅጣጫ በሕዳሴ መጀመሩንም አብስረዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top