
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ምርቃት ላይ በግድብ ግንባታው ወቅት በአመራርነት አበርክቶ የነበራቸው አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የክብር ኒሻን ተሸልመዋል፡፡
የክብር ኒሻን የተሸለሙት ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን አማካለኝ ከህዳር 2004 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የፕሮጀክቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣
ኢንጂነር ከማል አህመድ ሱለይማን ከሚያዚያ 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የፕሮጀክቱ የኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ
አቶ በላቸው ካሳ ወልዴ በምክትል ሥራ አስኪያጅ ማዕረግ የፕሮጀክቱ ሳይት አስተባባሪ
ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”




