
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የማደግ መሻት በላባቸው፣ በእንባቸው፣ በደማቸው እና በክብራቸው ያሳኩበት ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ህዳሴ ግድብ የዐባይ ልጆችን አንድ የሚያደርግ የኢትዮጵያውያን የፅናት ሽልማት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የኢትዮጵያ የቀጣይ ጊዜ ታላላቅ ስኬቶች ጅማሮ ነው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”