ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ የምታደርውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች

ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ የምታደርውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች


ዴንማርክ የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱን ክሮግስትራፕ ገለጹ።

አምባሳደሩ እንደገለፁት የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በዴንማርክና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራና የላቀ አጋርነት ማሳያ ነው።

የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ቀጣይነት ላለው የኢትዮጵያ ዕድገት ወሳኝ ምዕራፍ  መሆኑን አምባሳደሩ ተናግረዋል::

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂን ተግባራዊ በማድረግ ንፁህና አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል::

ዴንማርክ በንፋስ ኃይል ማመንጨትና በዘላቂ የኃይል አጠቃቀም ረገድ ያላትን ሰፊና የበለጸገ ልምድ በመጠቀም የኢትዮጵያን የኃይል ስርዓት ለማዘመን አስተዋጽኦ በማበርከቷ ኩራት እንደሚሰማቸው አምባሳደሩ ተናግረዋል።

ይህ የሁለቱ ሀገራት ትብብር የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደጉም በላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አብራርተዋል። ፕሮጀክቱ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በንጹህ ኢነርጂ አቅርቦት ረገድ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አምባሳደሩ አስረድተዋል።

ዴንማርክ ወደፊትም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ዘርፍ ለማልማትና ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያን የአረንጎዴ አሻራ ለማስቀጠል እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያከናውነውን የኢነርጂ ልማት ዴንማርክ እንደምትደግፍ አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top