የጣቢያውን የኮንክሪት ሙሌት ሥራ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

የጣቢያውን የኮንክሪት ሙሌት ሥራ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ማስቀመጫ መሰረት የኮንክሪት ሙሌት ሥራን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ዘርፍ የራስ ኃይል ግንባታ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ኃ/ጊዮርጊስ እንደገለጹት የኮንክሪት ሙሊት ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ከመከላክያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ጋር ስምምነት በመፈጸም ወደ ሥራ ተገብቷል።

በዚህም እስከአሁን የአንድ ትራንስፎርመር፣ የ62 ኮለሞች እና 173 ፓዶች የኮንክሪት ሙሌት ሥራ መጠናቀቁን አብራርተዋል።

የቀሪ 73 ፓዶችና የሦስት ትራንስፎርመሮች ማስቀመጫ መሠረት የኮንክሪት ሙሌት ሥራዎች በቀጣይ ቀናት በማጠናቀቅ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራውን ለመጀመር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የመከላክያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት 1 ሺ ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ለማቅረብና የሁለት ወራት ርዝማኔ ያለው ከተቋሙ ጋር ስምምነት ፈጥሮ የኮንክሪት ሙሌት ሥራው መጀመሩን ከአሁን ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top