በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ሀብት ስልጠናና ልማት መምሪያ ከአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመቀናጀት ያዘጋጀው የአመራር ሥርዓተ ልማት ሰነድ ለውይይት ቀረበ።
የተቋሙ የሰው ሀብት ስልጠናና ልማት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድወሰን ካሳ (ዶ/ር) እንደገለፁት ወርክሾፑ የተዘጋጀው ከተቋሙ የሥራ መሪዎች እና ባለሙያዎች በሰነዱ ላይ ተጨማሪ ግብአት ለመሰብሰብ ነው።
የአመራር ልማት ሰነዱ ዘጠኝ ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት እንዳሉት የገለፁት ዳይሬክተሩ የኮርፖሬት ስትራቴጂ ትንተና፣ የብቃት ወይም ኮምፒተንሲ ልየታ እና የሞጁል ዝግጅቶችን አካቷል ብለዋል፡፡
የአመራር ልማቱ ከአፍሪካ የአመራር ልቀት አካዳሚ ጋር በመሆን ተግባራዊ ሲደረግ ከላይ እስከ ታች የተናበበ ስትራቴጂያዊ አመራር ለመፍጠር እንደሚያስችል ተናግረዋል።
የአመራር ሥርዓተ ልማት ሰባት የብቃት ፕሮግራሞች ያሉት ሲሆን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የ18 ወራት ጊዜ እንደሚወስድ ተገልጿል።
14 ሞጁሎችን ያካተተው ይህ ሰነድ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠናዎችን በማካተት ለተቋሙ የሥራ መሪዎች የሚሰጥ ይሆናል።
በወርክሾፑ ላይ የተቋሙ የሥራ መሪዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የሥራ አመራር ስርዓተ ልማት ሰነዱን የሚያዳብሩ ግብአቶች አቅርበዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



