የግዥ ሥርዓቱን ለማዘመን ዲጂታይዜሽን እንደ መፍትሔ! 💻📜

የግዥ ሥርዓቱን ለማዘመን ዲጂታይዜሽን እንደ መፍትሔ! 💻📜

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግዥ ሂደቶቹን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ወረቀት አልባ ለማድረግ “ፔራጎ ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ” ከተሰኘ ሀገር በቀል ኩባንያ ጋር ሥራ ሊጀምር ነው፡፡

ይህ ዘመናዊ ሲስተም ምን ፋይዳ አለው? 🤔

ወረቀት አልባ አሠራር፦ የተቋሙን ሥራዎች በዲጂታል ሥርዓት በመምራት የአሠራር ችግሮችን በላቀ ፍጥነት ለመፍታት ያስችላል። 📄🚫

ግልጽነትና ተጠያቂነት፦ የግዥ ሂደቱ በግልጽነትና በተጠያቂነት እንዲመራ ከማድረጉም ባለፈ ለሦስተኛ ወገን የሚፈለጉ መረጃዎችን በወቅቱ ለማቅረብ ይረዳል። 🔍✅

የሳይበር ደህንነት፦ ሲስተሙ የሳይበር ደህንነት ፍተሻ ተደርጎበትና ከነባር የግዥ ሕጎችና ደንቦች ጋር ተናቦ የሚተገበር ነው። 🛡🔒

የፕሮጀክቱ ሂደት ⏳

የ21 ወራት የቆይታ ጊዜ ያለው ይህ ፕሮጀክት የሥልጠናና የድጋፍ ሥራዎችን ጨምሮ ሲስተሙን ከሌሎች የተቋሙ አሠራሮች ጋር የማናበብ ሥራዎችን ያጠቃልላል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዚህ በጀት ዓመት የተለያዩ አሠራሮቹን ከማኑዋል ወደ ዲጂታል ሥርዓት የመቀየር ተግባርን በልዩ ትኩረት እያከናወነ ይገኛል። 🚀✨

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top