የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ እና ለዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት መስማማቷን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
ይህ ስምምነት ለሀገራችን ምን ይዞ ይመጣል?
🔹 ዘመናዊ አሠራር፦ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን የአውቶሜሽን ሥርዓት ለማዘመን እና አዲስ የብሔራዊ ግሪድ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ለመገንባት ይውላል።
🔹 ጂኦተርማል ኃይል፦ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል (የከርሰ ምድር እንፋሎት) ኃይል ለማመንጨት አዲስ የማዕቀፍ ስምምነት ተደርጓል።
🔹 የተሻሻለ አገልግሎት፦ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን በ 50 በመቶ በመቀነስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የተሻለ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል።
🔹 አረንጓዴ ልማት፦ የካርቦን ልቀትን በ150 ሺህ ቶን በመቀነስ የአካባቢ ጥበቃ ጥረታችንን ያግዛል። 🌱🌍
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በአውሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲዎች (AFD) በትብብር የሚተገበር ሲሆን የሀገራችንን የኢነርጂ ዘርፍ ወደ ተሻለ ዲጂታል ከፍታ የሚያሸጋግር ነው።
ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል እያበራች ትቀጥላለች! 💡🇪🇹
