የግንባታ ማሽነሪዎችን በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ሥር ማንቀሳቀስ የሚኖረው ጉዳት

የግንባታ ማሽነሪዎችን በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ሥር ማንቀሳቀስ የሚኖረው ጉዳት

? የኤሌክትሪክ ዥረት (current) የብረት ይዘት ያላቸው ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁሶች ላይ በቀላሉ ስለሚተላለፍ እና ከኤሌክትሪክ ጋር በቀጥታ ስለሚገናኝ በማሽነሪዎቹም ሆነ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ በማሽነሪዎቹ እንቅስቃሴ የተነሳ አየሩን ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ሊያደርገው ይችላል፡፡

? ከከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ጋር መቀራረብ ከፍተኛ የኤሌክትሮ ማግኔቲክ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህም የኮሙዩኒኬሽን፣ የመቆጣጠሪያ እና የማንቂያ መሳሪያዎች በአግባቡ እንዳይሰሩ በማድረግ ማሽኖች ያልተጠበቀ ባህርይ እንዲያሳዩና እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል፡፡

? ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በከፍተኛ ሙቀት፣ በንፋስ እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ሊረግቡ ስለሚችሉ ከመስመሮቹ ጋር ድንገተኛ መነካካት በመፍጠር አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

? የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እንደ መካከለኛ እና ዝቅተኛ የስርጭት መስመሮች ኃይል በማያስተላልፍ ጎማ ወይም ኢንሱሌተር ስለማይሸፈኑ ኤሌክትሪክ በቀላሉ ወደማሽነሪዎቹ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ አደጋ ተከስቶ ማሽነሪውን ለመንቀሳቀስ ቢፈለግ እንኳ የማሽነሪው ጎማዎች እንዲቃጠሉ ስለሚያደርግ በጥቅሉ የማሽነሪዎች ሙሉ ቃጠሎ እና የሰው ህልፈት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡

? በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚደርስ ጉዳት ኃይል እንዲቋረጥ ከማድረግ ባለፈ የታወቆች መውደቅ በአቅራቢያቸው የሚገኙ ህንፃዎች እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል፡፡

? ስለሆነም ወደ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹ ቀርቦ ማሽነሪዎችን አለማንቀሳቀስ፣ የግድ ከሥራቸው የሚሰራ ነገር ሲኖር ኃይል መቋረጡን ማረጋገጥ፣ የቅርበትን/የርቀትን መጠን የሚያሳይ ምልክት ማስቀመጥ፣ ማሽነሪዎችን በቀጥታ በሰውነት ላለመንካት መጠንቀቅ እና የአስቸኳይ ጊዜ የጥንቃቄ ርምጃዎችን መተግበር ያስፈልጋል፡፡

Scroll to Top