በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች  በእስራት ተቀጡ።

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች  በእስራት ተቀጡ።

በደቡብ ወሎ ዞን ‎በቃሉ ወረዳ 07 ቀዲዳ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቀዲዳ በተባለ ቦታ 132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ታወር ብረት በመፍታት የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች የሰባት ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ግለሰቦቹ ተገቢው ቅጣት ሊወሰንባቸው የቻለው በኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን አውታር ላይ የስርቆትና ጉዳት ማድረስ ወንጀል በተፋጠነ የህግ ስነ-ስርአት አማካኝነት መሆኑን  በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ግለሰቦቹ በኃይል ማስተላለፊያው ላይ ባደረሱት የስርቆት ጉዳት በኮምቦልቻ፣ በደሴ ከተሞችና በ5 አጎራባች ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ ምክንያት ሆነዋል።

በተጨማሪም ከአቀስታ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሃይል የሚያገኙ የምዕራብ ወሎ ወረዳዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረግ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ገልጿል።

እነዚህ ግለሰቦች ኃይል እንዲቋረጥ ከማድረጋቸው ባሻገር 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ጉዳት ማድረሳቸውንም ነው ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ያስታወቀው።

የአቃቤ ህግን የሰነድና የሰው ማስረጃ እንዲሁም የተከሳሾችን የምስክር ቃል ተቀብሎ ሲመርምር የቆየው ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፍተኛ በማለት ተከሳሾችን ያርማል ሌሎችንም  ያስተምራል ያለውን የሰባት አመት ጽኑ እስራት  በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ወስኖባቸዋል።

መረጃውን ያገኘነው ከደቡብ ወሎ ዞን መምሪያ ኮሙኒኬሽን ነው

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top