የጂ አይ ኤስ ብሬከሮች ቅየራ ከኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ይፈታል

የጂ አይ ኤስ ብሬከሮች ቅየራ ከኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ይፈታል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እያከናወነ ያለው የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የማዘመን ሥራ የጣቢያዎቹን አሰራር በማዘመን በደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአገልግሎቱ የሻሸመኔ ሪጅን የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ አቶ ጅብሪል ሩቤ እንደገለፁት የጂ አይ ኤስ መቆጣጠሪያ ቅየራ መከናወኑ የጣቢያቹን አቅም በማሳደግ ለህብረተሰቡ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡

በሻሸመኔ ማከፋፈያ ጣቢያ የ33 ኪሎ ቮልት መቆጣጠሪያ ከዚህ በፊት ተቀይሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጅብሪል በአሁኑ ወቅት ደግሞ የ15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር መቆጣጠሪያዎችን ወደ ጂ አይ ኤስ መቆጣጠሪያ የመቀየር ሥራ እየተከናወን ይገኛል ብለዋል፡፡

በአገልግሎቱ የሲዳማ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ በበኩላቸው የማከፋፈያ ጣቢያ መቆጣጠሪያዎች የአገልግሎት ጊዜ እና የሚሰሩበት ዘዴ በማከፋፈያ ጣቢያዎች ለሚፈጠሩ የኃይል መቆራረጦች አንድ ምክንያት እንደሚጠቀሱ ገልፀዋል፡፡

በሪጅኑ ከሚገኙ አራት ማከፋፈያ ጣቢያዎች መካከል በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በይርጋለም አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ መቆጣጠሪያዎችን በዘመናዊ ዕቃዎች የመቀየር ሥራ ስለመጀመሩ ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል በአንድ ወጪ መስመር ተደርበው ኃይል ሲያገኙ የነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች አሁን በተጀመረው የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ቅየራ ሥራ ለየብቻቸው የሚወጡበትን ዕድል እንደሚፈጥርም አቶ አበበ ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ የብሬከር ቅየራው ከኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከደንበኞች ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሁለቱ ተቋማት ሲያጡት የነበረውን ገቢ በማስተካከል በኩል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ እንደገለፁት ሁለቱ ተቋማት ለህብረተሰቡ ያልተቆራረጠ ኃይል ለማቅረብ በቅንጅት እየሰሩ ናቸው፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር
↠https://twitter.com/EEPethiopia
ሊንክዲን↠
https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
ዩትዩብቻናል↠
https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et

Scroll to Top