የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግቦችን ለማሳካት የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን ገለፁ።
የ”ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030″ ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስትራቴጂው ይፋዊ ማብሰሪያ ወቅት እንደገለጹት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግቦች እንዲሳኩ መሠረታዊና አስቻይ ሁኔታዎች መካከል የመጀመሪያውና ዋነኛው የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ነው።
የኤሌክትሪክ ኃይል ለዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት እንደምግብ ነው ብለዋል።
የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚፈልጉ በመሆናቸው በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት ግድ እንደሚል አስገንዝበዋል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


