የዘርፉ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀመረ

የዘርፉ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀመረ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና የማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን በአርባ ምንጭ ከተማ  መገምገም ጀምሯል።

በዘርፉ የቴክኒክ ድጋፍ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አበባው ያለው ግምገማው ሲጀመር እንደተናገሩት በአፈፃፀም ግምገማው ላይ የሁሉም ሪጅኖች የዕቅድ አፈጻጸም ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እና ያጋጠሙ ችግሮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ይካሄዳበታል።

ከዚህ በተጨማሪም እየተከናወኑ ስላሉ የተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎች፣ ለሪጅኖች እየተደረገ ስላለው የቴክኒካል ድጋፍና በሳፕ አተገባበር ላይ ስለሚስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችና እያጋጠሙ ስላሉ ተግዳሮቶች ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በግምገማው ላይ የሚሳተፉት የሪጅኖቹ  የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች በትላንትናው ዕለት የሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ፣ የወላይታ ሶዶ ቁጥር አንድ እና ሁለት የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ጉብኝት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

Scroll to Top