የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ የፋይናንስ እና ግዥ ሥርዓቱን ለማሻሻል እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡
የዘርፉ የፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የፋይናንስ እና ግዥ አፈፃፀም እንዲሁም በ2018 ዕቅድ ዙሪያ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ውይይቱ የተካሔደው ተቋሙ ሁሉም የሥራ ዘርፎች እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ የፋይናንስ ሥራቸውን አጠናቀው ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ ነው።
መድረኩ የዘርፉ የፋይናንስና ግዥ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በቀሩት ጥቂት ቀናት ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ሥራዎቻቸውን እንዲያጠናቅቁ ለማድረግ ያለመ ነው።
በዘርፉ የፋይናንስና ግዥ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ዮሴፍ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለፁት የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመት በርካታ ፕሮጀክቶችን ሲያከናውን ቆይቷል።
መምሪያው የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት በፋይናንስና ግዥ የአሰራር ሥርዓት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ቀሪ ሒሳቦችን ለመዝጋት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ዘርፉ በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ያለውን የፋይናንስ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓትና ቅልጥፍና ማዘመን ይገባል።
በ2018 በጀት ዓመት የዘርፉን የፋይናንስና ግዥ ሥራዎች ቅንጅታዊ የአሰራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት ለመተግበር መታቀዱን አቶ ሙሉቀን ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ የዘርፉ የፋይናንስ አፈፃፀም ላይ ውይይት መደረጉና የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ለተሻለ የሥራ አፈፃፀም የሚያነሳሳ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በ2018 በጀት ዓመት የዘርፉን ውጤታማነት ከፍ የሚያደርጉ ሥራዎችን ለማከናወን ከወዲሁ መዘጋጀታቸውንም ነው ያብራሩት።
በቀሪዎቹ ቀናት ተቋሙ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የዘርፉ የፋይናንስ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”