ኢትዮጵያ ለነጠላ የኢነርጂ ገበያ ትግበራ እየሰራች ነው

ኢትዮጵያ ለነጠላ የኢነርጂ ገበያ ትግበራ እየሰራች ነው

ኢትዮጵያ ጎረቤቶቿን በኤሌክትሪክ ኃይል በማስተሳሰር ለነጠላ የኢነርጂ ገበያ ትግበራ መሠረት መሆኗን የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ፡፡

የህብረቱ የመሠረተ ልማትና ኢነርጂ ዳይሬክተር ካሙጊሻ ካዛውራ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ጁቡቲ፣ ኬኒያ እና ከቀሪ ጎረቤቶቿ ጋር የኃይል ትስስር እየፈጠረች  ነው፡፡

የአፍሪካ የኤሌክትሪክ የነጠላ ገበያ ከፍተኛ የቴክኒክ ግምገማ ላይ ለኢትዮጵያ ጥረቶች እውቅና የሰጡት ዳይሬክተሩ ይህም ለአፍሪካ ህብረት የነጠላ ኢነርጂ ገበያ ትግበራ አቅም እየሆነች መምጣቷን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top