የውስጣዊ ፍስሃ፥ ደስታ፣ እንባ–ሲቃ፣ ሳቅ፣ ብርሃን የዘመናት የቁጭት ስሜት፣ የስኬት ተድላ፤ አሁናዊ የሚሰማኝ ስሜት!!

የውስጣዊ ፍስሃ፥ ደስታ፣ እንባ–ሲቃ፣ ሳቅ፣ ብርሃን የዘመናት የቁጭት ስሜት፣ የስኬት ተድላ፤ አሁናዊ የሚሰማኝ ስሜት!!

በቅድሚያ፥ የሀገሬ ኢትዮጵያ የኔ ትውልድ ዓድዋ፣ የላቀ የታሪክ ምዕራፍ–ታሪክ ቀያሪ  ጉዞ አካል ላደረገኝ  ፈጣሪ ተመስገን! 🙏🏾

የዓመታት ምኞት፥ የዘመናት ፅኑ ሕልም፣ የመጪው ትውልድ ደማቅ ብርሃን እውን ሆኖ በአዲስ ዓመት መባቻ ከላቀ ገፀ-በረከት ጋር አዲስ ዓመቱን ስንቀበል፥ ድርብ ደስታ ነው። እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን አደረሰን።

ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፥  እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን ደስ አላችሁ።  እንኳን በደስታ ሲቃ ለምንቀበለው አዲስ ዓመት አደረሳችሁ።

እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ፥ ለትውልድ የምናወርሰው መቻልን፣ ብርታትን እና የልማት አርበኝነትን ነው። የተጣመመ ትርክት አቃንተን፥ በዕዳ  የተረከብነውን ለውጠን ወረት እና ምንዳን እናስረክባለን::

እንኳን ደስ አለን!
አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top