
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት የዋዜማ መርሃግብር በድሮን ትርኢት እና በርችት ዝግጅቶች በደመቀ ድባብ ተከናውኗል።
የዋዜማ መርሀግብሩ የተለያዩ ህብረ ቀለማዊ ትርኢቶች ቀርበውበታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
ዛሬ የሀገራት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የግድቡ ምርቃት በይፋ የሚከናወን ይሆናል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

