የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጣ

የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጣ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ ለሚያስገነባው ባለ 66 ወለል ዘመናዊ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ዓለም አቀፍ  ጨረታ አውጥቷል።

አጠቃላይ ግንባታው በ20 ሺህ 792 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፍ ሲሆን ሲጠናቀቅ 208 ሺህ 724 ካሬ ሜትር የሆነ አጠቃላይ የወለል ስፋት እና 345 ነጥብ 5 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል።

በአዲስ አበባ የፋይናንስ ማዕከል ተብሎ በተለየው በሜክሲኮ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ሕንፃ ዲዛይኑ በተቋሙ እና በአማካሪ ድርጅት በኩል የተዘጋጀ ሲሆን አሸናፊው ተቋራጭ ግንባታውን ብቻ የሚያከናውንበት የውል ዓይነት ነው።

የወጣው ጨረታ የግንባታውን የስራ ዝርዝር እና ግንባታውን ለማከናወን ተቋራጮች ሊያሟሉት የሚገባውን የፋይናንስና የቴክኒክ መስፈርት በዝርዝር የሚያመለክት ነው።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች ያለፉትን አምስት ዓመታት የኦዲት ሪፖርታቸውን እንዲሁም በአማካይ ቢያንስ 230 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓመታዊ ገቢ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው የጨረታ ሰነዱ ያመለክታል።

ከቴክኒክ አንፃር ደግሞ ቢያንስ ለ10 ዓመታት በግንባታ ላይ ልምድ ያላቸውና እያንዳንዳቸው ቢያንስ 370 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያላቸው ሦስት ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ መሆን ይኖርባቸዋል።

የንድፍ እና የግንባታ ክትትል አማካሪ በመሆን ዳር አል-ሃንዳሳ ነው።

የግንባታውን ወጪ በተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች ለመሸፈን ተቋሙ አማራጮችን እያየ  ሲሆን የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ አጠቃላይ የግንባታው ዋጋ የሚገለጽ ይሆናል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች  ስለግንባታው ወጪና ሌሎች መረጃዎች የወጡት መረጃዎች በተቋሙ በኩል ያልወጡና የተሳሳቱ እንደሆኑ ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስና ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top